Substance abuse counselling

It all starts with simple use of drugs just to have fun; recreational use. And you still think that you control the outcomes but through time the drugs change how your brain and body works, and before you know it you became addicted. But here put in your mind that drug abuse and addiction are two different terms. Drug abuse is the misuse of drug (legal or illegal) in a way that you are not supposed to. Addiction is when you want to stop but you can’t.

Substance abuse counseling is a comprehensive mental health field related with helping individual to recover from drug or alcohol addiction. While much focus is on the substance abuse itself, substance abuse counseling also seeks to address related issues in social, emotional, occupational, and mental health functioning. A foundational belief of substance abuse counselors is that addiction is a disease but that it is highly treatable given the appropriate treatments, interventions and time.

 

የሱስ ማገገሚያ ምክክር

ብዙዎቻችን በሆነ ነገር ሱስ እንደተያዝን የምንረዳው ያን ነገር ስነተወው እና በዚህ ምክንያት  የተለመደውን የቀን ተቀን ተግባራችንን መከወን ሲሳነን ነው፡፡

ሁሉም ነገር የሚጀመረው ቀለል ተደርጎ ለጊዜያዊ መዝናናት ነው፤ ሲጋራው፣ መጠጡ፣  ጫቱ...ወዘተ እና እኛም የምናስበው ሂደቱ በቁጥጥር ስራችን እንደሆነ ነው፤ሆኖም በጊዜ ሂደት እነዚህ አደንዛዥ ዕጾች ሰውነታችንን እና ጭንቅላታችንን ይቆጣጠሩታል፤ በህይወታችን ላይም የተለያየ ተፅዕኖ ያሳድሩብናል፡፡ ቢሆንም እዚህ ጋር ግን አንድ ነገር ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል ትክክለኛ ያልሆነ የመድሃኒት (እፅ) አጠቃቀም (Substance abuse) እና ሱስ (Addiction) ይለያያል፡፡ የመጀመሪያው አንድን መድኃኒት ከተገባው ወይም በትዕዛዙ መሰረት ሳንወስድ ስንቀር ሲሆን ሁለተኛው ወይም ሱስ የምንለው ደግሞ መድሃኒቱን (እፁን) መውሰድ ፈልገን ማቆም ሳንችል ሲቀር ነው፡፡

የሱስ ማገገሚያ ምክክር ስሙ በራሱ እንደሚያመለክተው በተለያዩ አደንዛዥ ዕፅ ሱስ ውስጥ የወደቁ ሰዎችን ከሱሳቸው ለማለቀቅ የሚሰጥ የምክክር አገልግሎት ነው፡፡ እዚህ ጋር አንድ ነገር እንድትገነዘቡ እንፈልጋለን ሱስ በሽታ ነው፤ እንደ አብዛኞቹ በሽታዎች ደግሞ ትክክለኛውን መድኃኒት (ምክክር) የሚያገኝ ከሆነ የመዳን እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡