Group counseling

Group therapy could be effective for several psychological problems, for instance depression, traumatic stress, panic disorder, bipolar disorder, obsessive-compulsive disorder, social phobia and substance addiction. Among the many advantages of group counseling the following are some; it helps to give and receive support to one another, group members can be role model to each other, it is relatively affordable in terms of cost and finally it allows the counselor to see how the members react with other people in a real social situation.

In this type of counseling the group members could range from 3 to 12 individuals (could be more), in which the group could meet for weekly for an hour or two; in a setting where the chairs are arranged in a large circle so that each member can see and listen every other person in the group. A session might begin with members of the group introducing themselves and sharing why they are in group therapy or what brought them to the group counseling, members also share their experiences and progress since the last meeting.

The counselor conduct the counseling process with the principles like the installation of hope, universality, imparting information, altruism, development of socialization techniques, imitative behavior, interpersonal learning, group cohesiveness, existential factors and catharsis.

 

የቡድን ምክክር

በዚህ የምክክር ዓይነት አንድና ከዛ በላይ የሆኑ የስነ-ልቦና አማካሪዎች ተመሳሳይ የሆነ የስነ ልቦና ችግር ያለባቸውን ሰዎች አንድ ላይ በማድረግ የሚሰጥ የምክክር አገልግሎት ነው፡፡

የቡድን ምክክር ለተለያዩ የስነ-ልቦና ችግሮች መፍትሄ ሊሆን ይችላል፤ ከእነዚህም መካከል ድባቴ፣ ጭንቀት፣ የባህርይ መዛባት እና ሱስ ይገኙበታል፤ ሰዎችም ይህን የምክክር ዓይነት እርስ በእርስ መረዳዳትን እና መማማርን ስለሚያበረታታ፣ ወጪ ቆጣቢ በመሆኑ እንዲሁም በሰዎች መካከል ማህበራዊ መስተጋብራቸው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ በመርዳቱ ምክንያት ይመርጡታል፡፡

በቡድን ውይይት የቡድኑ አባላት በአማካይ ከ 3 እስከ 12 (በትንሹ ሊበልጥም ይችላል)  ሲሆኑ፤ በአንድ ክፍል ውስጥ ክብ በተደረደሩ ወንበሮች ላይ በመቀመጥ በሳምንት በትንሹ ለአንድ ሰዓት በመገናኘት ምክክር ያደርጋሉ፡፡  አንድ ክፍለ ጊዜ የሚጀመረው የቡድኑ አባላቶች  ራሳቸውን በማስተዋወቅ እና ለምን ወደ ምክክሩ እንደመጡ ለቀሩት የቡድን አባላት በመናገር ይጀምራሉ፡፡ የስነ-ልቦና ባለሙያው ደግሞ የምክክር ጊዜውን የተለያዩ መርሆችን ማለትም ተስፋን ማስረጽ፣ ተመሳሳይ ድጋፍ፣ መረጃዎችን በግልጽነት መወያየት እና መለዋወጥ፣  አርስ በእርስ መረዳዳት እና መማማር፣የተግባቦት ክህሎትን ማሳደግ፣ እና ስሜትን መግለጽ ላይ በመመስረት ምክክሩን ያደርጋል፡፡